Skip to main content
news2

የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ከከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 'በጎነት ለጤናችን' የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር በዞኑ አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ በመካሔድ ላይ ነው። በጎነት ለጤናችን በተሰኘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር የስኳር፣ የደም ግፊት እና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምርመራ ለ1000 ሰዎች በነፃ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። መርሀ ግብሩን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መለሰ አጭሶ በይፋ አስጀምረውታል።