የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል EHAQ ክላስተር የ2ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ተገመገመ። መጋቢት 16/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ትስስር (EHAQ) የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ክላስተር የ2017 ዓ.ም የ2ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል። በ4ኛው ዙር የኢትዮጲያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ትስስር (4th- Cycle EHAQ) መረጃን መሰረት ባደረገ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ (Evidence Based Care) የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ የጨቅላ ህፃናት፣የቀዶ-ጥገና፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ፣የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን ህክምና፣የነርሲንግ ክብካቤ አገልግሎት እና በጥምረቱ መሪ በዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል የተከናወኑ የድጋፋ ክትትልና ሜንተርሽፕ እንዲሁም ሌሎች በጥምረቱ ሆስፒታሎች የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት የ2017 ዓ.ም የ2ኛ ሩብ አመት አጠቃላይ ሪፖርት አፈፃፀም ቀርቦ ከተሳታፊዎች ጋር በዝርዝር ውይይት ተደርጎበታል። የግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራአስኪያጅ ዶ/ር ደረበ ዮሐንስ እንደተናገሩት የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ፍላጎት ለማሻሻል፣ የአገልግሎት ጥራቱን ለማሳደግና በሆስፒታሎች መካከል ጠንካራ ትስስርን መፍጠር እንዲቻል የሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት(EHAQ) ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀው በቀጣይም የተጀመሩ መልካም ስራዎችን ለማስቀጠል እና የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት በሆስፒታሉ በኩል የሚደረጉ የድጋፍ እና ክትትል ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ገልጸዋል። በመድረኩም የጥምረቱ አካል የሆኑ ሆስፒታሎች በቀጣይ በቅንጅትና በትብብር ለመስራት በሚያስችላቸው ተግባራት ዙሪያ የጋራ መግባባት በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል። በግምገማ መድረኩ ላይ ከዞኑ ጤና መምሪያ፣የጥምረቱ አባል ከሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እና ከዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል የስራ ሀላፊዎችና ዘርፉ የሚመለከታቸዉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።