Skip to main content
news13

በዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል የCT_Scan ማሽን አገልግሎት ማስጀመሪያና የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከል ግንባታ መሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሃግብር ተካሄደ። በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የጋራ ትብብር (public and private partnership የጤና ፖሊሲ የጤና ሚኒስተር በBMY Technologies PLC እና በዶ/ር በጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል የሦስትዮሽ ስምምነት የተገኘው የCT_SCAN ማሽን የአገልግሎት ማስጀመሪያና የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሃግብር መካሄዱም ነው የተመለከተው። በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታና የእለቱ ክቡር እንግዳ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ኢትዮጵያን በብልጽግና ማማ ላይ ለማስቀመጥ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል ነው ያሉት። የተቋማት ግንባታ ሀገርን ለማስቀጠል ወሳኝ መሆናቸውን የጠቀሱት ዶክተር ደረጃ ዱጉማ ሆስፒታሎች ዘርና ቀለም ሳይለዩ ለሁሉም ህሙማን ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጣት እውነተኛ ህብረ ብሔራዊነት የሚታዩባቸው ተቋማት በመሆናቸው አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል በሚደረገው ጥራት የጤና ሚኒስቴር በሚያስፈልገው ሁሉ ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ አንተነህ ፈቃዱ መንግስት የጤናውን ዘርፍ በማዘመን ተገቢውን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግና ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር እንደሀገርም እንደ ክልልም በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። የዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ለበርካታ ዜጎች አገልግሎት በመስጣት የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የተለያዩ ፈተናዎችን በመሻገር በጥራት አገልግሎት እየሰጣ እንደሚገኝ የገለፁት የተከበሩ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በዞኑና አካባቢው በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመፍታት በዛሬው አገልግሎት የጀመረው ሲቲ ስካንና መሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋልም ነው ያሉት። ሆስፒታሉ ሜዲካል ቱሪዝምን በአካባቢው እውን ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራት ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው የተናገሩት የተከበሩ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የሆስፒታሉ አጠቃላይ ማህበረሰብና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ከታከለበት ራዕዩን እውን ለማድረግ ያግዛልም ብለዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በክልሉ በሁሉም መዋቅር በጤናው ዘርፍ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልፀው በዚህም በዶ/ር ቦጋላች ገቡሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል እንደ ሀገር ሁለተኛ የሆነውን CT SCAN ማሺን ለአገልግሎት መብቃቱ የህዝብን ችግር በእጅጉ የሚፈታ እንደሆነ ተናግረዋል ። በክልሉ በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ መሰረታዊ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመፍታት ለህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት በቅንጅት እንደሚሰራ የተናገሩት አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የጤና ሚንስቴር በክልሉ በጤናው ዘርፍ መነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጠይቀዋል ። የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ በሆስፒታሉ የCT_scan አገልግሎት እና የoxygen plant project ግንባታ ስራ በይፋ በመጀመሩ የተሰማቸውን ልባዊ ደስታ በዞኑ ህዝብና አስተዳደር ስም ገልፀዋል። የጤና አመራራችን በሽታን በመከላከል እና አክሞ በማዳን ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ዙሪያ ማህበረሰባችን መሰረታዊ ግንዛቤ ኖሮት ሁሉም ዜጋ ከራሱ ጀምሮ የአካባቢዉን ንጽህና በመጠበቅ ጽዱ እና ለኑሮ ተስማሚ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር ለጤና ስርዓታችን ትርጉም ባለዉ መልኩ ለማሻሻል የጋራ ርብርብ መደረግ አለበትም ነው ያሉት ክቡር ዋና አስተዳዳሪው መንግሥት በአሁን ወቅት እያበረታታ ያለውን የመንግሥት እና የግል ካምፓኒዎች ትብብር public-private- partnership/ ሞዴል ተግባራዊ በማድረጉ ሆስፒታላችን የCT_scanን ማሽን ተጠቃሚ እንዲሆን ትብብር ላደረጋችሁ ለጤና ሚኒስቴር፤ ለክልላችን ጤና ቢሮ እና BMY technologies PLC ምስጋናዬ ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት የoxygen plant project የሆስፒታላችንን የህክሚና የአገልግሎት አሰጣጥ የበለጠዉን ለማሻሻል የሚያግዝ ሲሆን ሥራው ተጠናቆ ከጥቂት ወራት በኋላ ምርቱን ሲጀምር ለጎረቤት የጤና ተቋማት ጭምር የሚበቃ የoxygen ምርት በመስጠት መላውን የክልላችን ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል። በአጠቃላይ የሆስፒታላችንን የአገልግሎት አሰጠጥ በማዘመን እና አስፈላጊዉን የጤና መሰረተ ልማት በሟሟላት ሆስፒታላችንን center of excellence በማድረግ ከሚመለከተቸዉ ከክልል እና ከፌዴራል ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት ሆስፒታላችን ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንዲሆን የምንሰራ ይሆናል፡፡ ለዚህ ጥረት የክልላችን ጤና ቢሮ እና የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የተለመደውን እገዛ ከወትሮ በላቀ ደረጃ እንደሚታደርጉም ተማጽነዋል፡፡ የዶክተር ቦጋለች መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ደረበ ዮሐንስ በበኩላቸው ሆስፒታሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ አሰራርን በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የህብረተሰቡን የህክምና አገልግሎት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ በ2017 በጀት ዓመት ብቻ ሰፋፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል። በተላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሆስፒታላችን ለህሙማን ከሚሰጠው አገልግሎት አኳያ ተመራጭ እየሆነ በመምጣቱ የተኝቶም ሆነ የተመላላሽ ታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የተናገሩት ዶክተር ደረበ ዮሐንስ በዛሬው ዕለት በይፋ አገልግሎት የጀመረው የcT_SCAN እና የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት የoxygen plant project ሥራው አልቆ ከወራት በኋላ በማስመረቅ ከዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ባሻገር ፤ ከጎረቤት ሆስፒታሎች አልፎ ለመላው የክልላችን ህዝቦች የሚበቃ የoxygen ምርት የሚሰጥ መሆኑን በመግለፅ ለዚህ ስኬት የድርሻቸውን የተወጡ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋልም ነው ያሉት። በመርሃ ግብሩ የኢፌድሪ ጤና ሚኒስተር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የከምባታ ዞን መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተክሌ ስዩም፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች፣የከምባታ ዞን አስተባባሪ አካላት፣ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ራመቶ አቦ፣ የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ታረቀኝ ተስፋዬን ጨምሮ የሆስፒታሉ የሥራ ኃላፊዎች የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።