Chernet_Nuramo
በመርሃ-ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የመድኃኒትና ህክምና መገልገያ መሣርያዎች ዳይሬከረቶሬት የፋርማሲ አገልግሎት ኬዝ-ቲም ቡድን መሪ የሆኑት አቶ መኅቡብ ኑሪ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የሥልጠናዉ ዓላማ እና ግብ ላይ ያተኮረ ቁልፍ መልዕክት በማስቀመጥ ሥልጠናዉን ባይፋ አስጀምረዋል፡፡
በሥልጠናዉላይ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሁሉም ዞን ጤና መምሪያ፤ ልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት እና ሆስፒታሎች የተወጣጡ የፋርማሲ አስተባባሪዎች፤ባዮሜድካል እንጅኔሮች/ቴክኒሽያኖች እና ሌሎች ጤና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።
ሥልጠናዉስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ መካሄዱን የCPD Center አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዘላለም በቀለ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል CPD Center
ዱራሜ፤ ታህሳስ 17/2018 ዓ/ም